Сообщить об ошибке

Подтвердить права

Добавьте бота @sdsearchtestbot администратором ресурса, затем нажмите «Проверить».

Пожаловаться

Аватар TIKVAH-SPORT

TIKVAH-SPORT

@tikvahethsport
Вступить в канал
290671подписчиков / участников
0,0рейтинг
Каналтип ресурса
11.09.2026добавлен
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469
⚽ Спорт🌐 Амхарский📍 Эфиопия🔓 Публичный

Последние публикации

🖼Фото
“ አልቫሬዝ እኔን ለማሳገት ተሳትፏል ” “ ሀሰተኛ ውንጀላ ነው እክሳለሁ ” ኤድሰን አልቫሬዝ የሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን አምበል ኤድሰን አልቫሬዝ ሰው ለማሳገት ተሳትፏል በሚል ውንጀላ ቀርቦበታል። የዌስትሀም ዩናይትዱ አማካይ ኤድሰን አልቫሬዝ በበኩሉ የቀረበበትን የጠለፋ ክስ ውድቅ አድርጓል። ክሱን ያቀረበው አንድ የፊልም ባለሙያ ሲሆን በ 2024 ኤድሰን አልቫሬዝ እኔን ለማገት አሲሯል ሲል ገልፆ ነበር። በወቅቱ ሁለት ሰዎች መሳሪያ ይዘው አይኑን በመሸፈን እንዳገቱት የፊልም ባለሙያው ተናግሯል። የፊልም ባለሙያው ከተጨዋቹ ጋር ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ ያልተከፈለው 206ሺህ ዶላር ገንዘብ እንዳለው ገልጿል። በዛን ወቅት ክፍያ መጠየቁን እና በዚህ ምክንያት ከኤድሰን አልቫሬዝ ቤተሰብ ጋር ግጭት ውስጥ እንደገባ ተናግሯል። ኤድሰን አልቫሬዝ በበኩሉ የቀረበበትን ክስ ውድቅ በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል። @Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🖼Фото
🌻🙏እንኳን ለ2019 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።🌻🌻🌻 🌼አዲሱ አመት ለሁላችንም የደስታ እና የበረከት እንዲሁም አካዳሚዎች የለፋችሁበት ታዳጊ ፍሬያማ የሚሆንበት፣ የፕሪምየር ሊግ ቡድኖቻችን ደማቅ የውድድር ዘመን፣የጤና ቡድኖቻችን ደግሞ አንድነታችሁ እና ውድድራቹ የደመቀ የሚሆንበት፣ ስፖርተኛው ከውድድሩ በላይ ራሱን የሚያሸንፍበት አመት እንዲሆንላችሁ ዋናው ስፖርት መልካም ምኞቱን ያቀርባል!🌻 መልካም በዓል!🌻 😎😎😎😎
🖼Фото
ኢናኪ ዊሊያምስ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አግልሏል ! የጋና ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ኢናኪ ዊሊያምስ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን አስታውቋል። ኢናኪ ዊሊያምስ በሰጠው አስተያየት " ጋና የሰጠችኝ ከእግርኳስም በላይ ነው " ሲል ገልጿል። የ 32ዓመቱ አጥቂ ኢናኪ ዊሊያምስ ለጋና ብሔራዊ ቡድን 28 ጨዋታዎችን በማድረግ ሁለት ግብ ማስቆጠር ችሏል። ተጨዋቹ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር በሁለት አለም ዋንጫ እና አንድ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሳትፏል። @Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🖼Фото
የሊቨርፑል ተጨዋቾች ጉዳት ሁኔታ ? የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተሰላፊ ኮዲ ጋክፖ ዛሬ ልምምድ እንደሚጀመር አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ኮዲ ጋክፖ ለፉልሀም ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን አሰልጣኙ አሳውቀዋል። የብራዴሌይ ባርኮላ ሁኔታ ዛሬ እንደሚገመገም የገለፁት አሰልጣኙ ለጨዋታው ሊደርስ ይችላል ብለዋል። በሌላ በኩል ሁጎ ኤኪቲኬ በሻምፒየንስ ሊጉ ምድብ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ሊደርስ ይችላል ተብሏል። ሊቨርፑል ኤኪቲኬን በሻምፒየንስ ሊጉ ስብስብ ያስመዘገበው ይህንን ተስፋ በማድረግ መሆኑን አንዶኒ ኢራኦላ ተናግረዋል። @Tikvahethsport     @kidusyoftahe
🖼Фото
የፕሪሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል ! የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2026/27 የውድድር አመት የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የሀል ሲቲው አሰልጣኝ ሰርጅ ጃክሮቪች የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ተመርጠዋል። አሰልጣኝ ሰርጅ ጃክሮቪች ሀል ሲቲን እየመሩ በወሩ ያደረጓቸውን 2️⃣ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል። @Tikvahethsport     @kidusyoftahe

Продвижение